የሽምብራ ሽሮ ወጥ በአልጫ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'shimbra Shiro Wot, Alicha

የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት30 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 100 ግራም የሽምብራ ሽሮ ዱቄት (3 አነስተኛ ኩባያ)
  • 78 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2 አነስተኛ ኩባያ)
  • 75 ግራም ዘይት (2.25 አነስተኛ ኩባያ)
  • 11 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 3 ግራም እርድ (1 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 15 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 1100 ሚሊ ውሃ (1.1 ሊትር)
  • 6 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 የሻይ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን በዝቅተኛ እሳት ወርቃማ እስኪሆን ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3እርዱን ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለተጨማሪ 5 ደቂቃ ማብሰል።
  5. 5ተስማሚ መጠን ያለው ውሃ ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማፍላት።
  6. 6የሽምብራውን ሽሮ እንዳይጓጉል ያለማቋረጥ እያማሰሉ ቀስ በቀስ በመነስነስ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
  7. 7ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  8. 8ቃሪያ ጨምሮ ከእሳት ማውጣትና በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች