ባምያ አልጫ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Bameya Alicha
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት46 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 566 ግራም በርዝመቱ የተሰነጠቀ የተዘፈዘፈ ባምያ (3 ትላልቅ ኩባያ)
- 73 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (0.5 ትልቅ ኩባያ)
- 100 ግራም ዘይት (1.25 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 139 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (2 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 16 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (4 አነስተኛ ማንኪያ)
- 2 ግራም ኮረሪማ (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 22 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (3 የሻይ ማንኪያ)
- 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
- 1200 ሚሊ ውሃ (1.2 ሊትር)
አሰራሩ
- 1የባምያውን ጫፍ ቆርጦ በርዝመቱ መክፈል፤ በ1.5 ሊትር ውሃ ውስጥ ለ12 ሰዓት ዘፍዝፎ በወንፊት ማጠንፈፍና በቀዝቃዛ ውሃ ደጋግሞ ማጠብ።
- 2ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ቲማቲም ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማፍላት፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ጨው እና ኮረሪማ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 5ባምያውን ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማፍላት።
- 6ውሃ ጨምሮ ለ30 ደቂቃ ማብሰል፤ ቃሪያ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ ማውጣት።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025