ድፍን ምስር ወጥ በቀይ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Difin Misir Wot, Keye

የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት109 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 400 ግራም ድፍን ምስር (4 መካከለኛ ኩባያ)
  • 200 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (3.25 መካከለኛ ኩባያ)
  • 120 ግራም ዘይት (1.5 መካከለኛ የቡና ስኒ)
  • 30 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (2 የሾርባ ማንኪያ)
  • 15 ግራም ጨው (3 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 3500 ሚሊ ውሃ (3.5 ሊትር)
  • 88 ግራም በርበሬ (9 የሾርባ ማንኪያ)
  • 2 ግራም መከለሻ (0.5 የሻይ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1በትልቅ ድስት ውስጥ የተለቀመውን ድፍን ምስር ጥዶ ለ70 ደቂቃ መቀቀል።
  2. 2በሌላ ድስት ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ5 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3በርበሬ ጨምሮ ለ10 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4የተቀቀለውን ድፍን ምስር ከመረቁ ጋር አብሮ ጨምሮ ለ15 ደቂቃ ማፍላት።
  5. 5ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6መከለሻ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች