የሽምብራ ሽሮ ተጋቢኖ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Ye'shimbra Shiro Tegabino
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት40 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 140 ግራም የሽምብራ ሽሮ ዱቄት (2 መካከለኛ ኩባያ)
- 140 ግራም ዘይት (4 አነስተኛ ኩባያ)
- 100 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ኩባያ)
- 15 ግራም በርበሬ (1.5 የሾርባ ማንኪያ)
- 145 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (5.25 የሾርባ ማንኪያ)
- 12 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (3 አነስተኛ ማንኪያ)
- 8 ግራም ጨው (1.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 1150 ሚሊ ውሃ (1.15 ሊትር)
- 12 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 የሾርባ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
- 2ዘይት ጨምሮ አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 3በርበሬ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 4የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 5ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
- 6የቀረውን ውሃ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
- 7የሽምብራውን ሽሮ እንዳይጓጉል ያለማቋረጥ እያማሰሉ ቀስ በቀስ በመነስነስ ለ18 ደቂቃ ማብሰል።
- 8ጨው ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 9ቃሪያ ጣል አድርጎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025