የነጭ ማሽላ ገንፎ በቂቤ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'nech Mashila Genfo Be'kibe

ኢትዮጵያዊቁርስ26 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 300 ግራም የተፈተገ የነጭ ማሽላ ዱቄት (4 መካከለኛ ኩባያ)
  • 800 ሚሊ ውሃ (0.8 ሊትር)
  • 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 60 ግራም ቂቤ (10 የሾርባ ማንኪያ)
  • 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1የነጭ ማሽላ ዱቄቱን በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ መንፋት።
  2. 2ውሃውን ለ5 ደቂቃ ማፍላት።
  3. 3ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
  5. 5የተቀመጠውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እያከሉ ድስቱን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ20 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ሳህኑን በቅቤ መቀባትና ገንፎውን ሳህን ላይ ማድረግ።
  7. 7ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን መብሳት።
  8. 8የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስና በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች