ቡርሳሜ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Burusame
ኢትዮጵያዊቁርስምሳእራት20 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 480 ግራም ቆጮ (4.25 መካከለኛ ኩባያ)
- 170 ግራም ቂቤ (2.25 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 11 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ምጣዱን ወይም መጥበሻውን ማሞቅ።
- 2ቆጮውን በጋለው ምጣድ ላይ ጨምሮ ያለ ቅባት ለ18 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ጨው ጨምሮ በማፈሻ በሚገባ ማገላበጥ።
- 4የቀለጠውን ቅቤ በበሰለው ቆጮ ላይ ማፍሰስና እስኪፈረካከስ ለ2 ደቂቃ በሚገባ ማሸት።
- 5ከእሳት አውርዶ በሙቀቱ ማቅረብ (እንደ ምርጫ ከእርጎ ጋር)።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025