እንጀራ ፍርፍር በስጋ አልጫ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Enjera Ferfer Be'siga, Alicha
ኢትዮጵያዊቁርስምሳእራት32 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 291 ግራም የነጭ ጤፍ እንጀራ (1 መካከለኛ)
- 60 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1 መካከለኛ ኩባያ)
- 80 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ ኩባያ)
- 5 ግራም እርድ (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 166 ግራም የበሬ ስጋ (3.33 አነስተኛ ኩባያ)
- 20 ግራም ቅቤ (ግማሽ አነስተኛ ኩባያ)
- 10 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (2 የሻይ ማንኪያ)
- 13 ግራም ጨው (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 600 ሚሊ ውሃ (0.6 ሊትር)
አሰራሩ
- 1ሽንኩርቱን በዝቅተኛ እሳት ወርቃማ እስኪሆን ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
- 2እንዳይዝ ጥቂት ውሃ ጠብ እያደረጉ ማማሰል።
- 3ዘይት ጨምሮ አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 4እርዱን ጨምሮ እንዳይዝ ጥቂት ውሃ እያከሉ ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
- 5ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ስጋውን ጨምሮ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
- 7የተለካውን ውሃ ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማፍላት።
- 8ጨውና ቅቤ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 9የተቆራረሰውን እንጀራ ጨምሮ በሚገባ ማደባለቅ።
- 10ለ1 ደቂቃ ካበሰሉ በኋላ አውርዶ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025