የነጭ ዳጉሳ ገንፎ በቂቤ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Ye'nech Dagusa Genfo Be'kibe
ኢትዮጵያዊቁርስ16 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 200 ግራም የነጭ ዳጉሳ ዱቄት (5 አነስተኛ ኩባያ)
- 700 ሚሊ ውሃ (0.7 ሊትር)
- 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 60 ግራም ቂቤ (10 የሾርባ ማንኪያ)
- 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1የዳጉሳውን ዱቄት በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ መንፋት።
- 2ውሃውን ለ4 ደቂቃ ማፍላት።
- 3ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማፍላት።
- 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
- 5የቀረውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እየጨመሩ ድስቱን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ11 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ሳህኑን በቅቤ መቀባትና ገንፎውን ሳህኑ ላይ ማድረግ።
- 7ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን በማንኪያ መብሳት።
- 8የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስና በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025