የበቆሎ ገንፎ በቂቤ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'nech Bekolo Genfo Be'kibe

ኢትዮጵያዊቁርስ23 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 500 ግራም የበቆሎ ዱቄት (8.33 መካከለኛ ኩባያ)
  • 1500 ሚሊ ውሃ (1.5 ሊትር)
  • 8 ግራም ጨው (1.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 60 ግራም ቂቤ (10 የሾርባ ማንኪያ)
  • 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ የበቆሎውን ዱቄት መንፋት።
  2. 2ውሃውን ለ6 ደቂቃ ማፍላት።
  3. 3ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማፍላት።
  4. 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
  5. 5የቀረውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እየጨመሩ ድስቱን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ16 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ሳህኑን በቅቤ መቀባትና ገንፎውን ሳህን ላይ ማድረግ።
  7. 7ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን መብሳት።
  8. 8የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስና በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች