የቀይ ማሽላ ገንፎ በቂቤ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'keye Mashila Genfo Be'kibe

ኢትዮጵያዊቁርስ22 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 300 ግራም የተፈተገ የቀይ ማሽላ ዱቄት (4 መካከለኛ ኩባያ)
  • 1000 ሚሊ ውሃ (1 ሊትር)
  • 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 60 ግራም ቂቤ (10 የሾርባ ማንኪያ)
  • 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1የማሽላውን ዱቄት በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ መንፋት።
  2. 2ውሃውን ለ6 ደቂቃ ማፍላት።
  3. 3ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
  5. 5የተቀመጠውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እያከሉ ድስቱን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ14 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ሳህኑን በቅቤ መቀባትና ገንፎውን ሳህን ላይ ማድረግ።
  7. 7ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን መብሳት።
  8. 8የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስና በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች