የፉርኖ ዱቄት ገንፎ በቂቤ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'furno Duket Genfo Be'kibe

ኢትዮጵያዊቁርስ20 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 300 ግራም የፉርኖ ዱቄት (10 አነስተኛ ኩባያ)
  • 750 ሚሊ ውሃ (0.75 ሊትር)
  • 12 ግራም ጨው (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 75 ግራም ቂቤ (1 መካከለኛ የቡና ስኒ)
  • 14 ግራም በርበሬ (1.5 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1የፉርኖ ዱቄቱን በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ መንፋት።
  2. 2ውሃ በማብሰያ ድስት ውስጥ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
  3. 3ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማፍላት።
  4. 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
  5. 5የተቀመጠውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እያከሉ ድስቱን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ16 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ሳህኑን በቅቤ መቀባትና ገንፎውን ሳህን ላይ ማድረግ።
  7. 7ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን በማንኪያ መብሳት።
  8. 8የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስና በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች