የፍየል ስጋ ጥብስ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'fiyel Siga Tibs

ኢትዮጵያዊምሳእራት20 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 350 ግራም የአጥንት የፍየል ስጋ (2 ትላልቅ ኩባያ)
  • 100 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1 ትልቅ ኩባያ)
  • 60 ግራም ዘይት (10 የሾርባ ማንኪያ)
  • 22 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 አነስተኛ ኩባያ)
  • 15 ግራም ቂቤ (2.5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 9 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 15 ግራም ሚጥሚጣ (1.5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 2 ግራም ኮረሪማ (1 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 114 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (1 ትልቅ ኩባያ)
  • 3 ግራም ሮዝመሪ (1 የሻይ ማንኪያ)
  • 10 ግራም የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 50 ሚሊ ውሃ

አሰራሩ

  1. 1ስጋውን እና አጥንቱን በመካከለኛ መጠን መክተፍ።
  2. 2ዘይት አሙቆ ስጋውን ጨምሮ ያለማቋረጥ እያማሰሉ ለ13 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቲማቲም ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4ጨው እና ኮረሪማ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማማሰል።
  5. 5የጥብስ ቅጠል ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ቃሪያ መጨመር።
  6. 6ቅቤ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ ማውጣት።
  7. 7በሙቀቱ ከእንጀራ እና ከሚጥሚጣ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች