ጩካሜ በስጋ እና በጎመን፦ ካሎሪ እና አሰራር

Chukame Be'siga ena Be'gomen

ኢትዮጵያዊምሳእራት33 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 111 ግራም የተከተፈ የጎመን ቅጠል (1.5 ትልቅ ኩባያ)
  • 200 ግራም በስሱ የተከተፈ የበሬ ስጋ (1 ትልቅ ኩባያ)
  • 110 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 20 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 አነስተኛ ኩባያ)
  • 9 ግራም ጨው (ለወጡ) (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 87 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ ኩባያ)
  • 500 ሚሊ ውሃ (ለወጡ) (0.5 ሊትር)
  • 666 ግራም ቆጮ (6 መካከለኛ ኩባያ)
  • 105 ግራም ቂቤ (3 አነስተኛ ኩባያ)
  • 10 ግራም ጨው (ለቆጮው) (2 አነስተኛ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1ሽንኩርቱን ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2የበሬ ስጋውን ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ስጋው እስኪበስል ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3የተከተፈ ጎመን ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማፍላት፤ ጨው ጨምሮ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4ቃሪያ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አዋህዶ ወጡን ማውጣት።
  5. 5ቆጮውን በጋለ ምጣድ ላይ ለ5 ደቂቃ ማብሰል፤ ጨውና ቅቤ ጨምሮ ለ5 ደቂቃ እያሹ ማፈራረቅ።
  6. 6የቆጮው መሃል ላይ ጉድጓድ አውጥቶ የስጋና የጎመኑን ወጥ መሃሉ ላይ አፍሶ በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች