ጩካሜ በአደንጓሬ እና በጎመን፦ ካሎሪ እና አሰራር

Chukame Be'adenguare ena Be'gomen

ኢትዮጵያዊምሳእራት169 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 170 ግራም የተከተፈ የጎመን ቅጠል (3.5 ትላልቅ ኩባያ)
  • 141 ግራም ቀይ ቦሎቄ/አደንጓሬ (1 መካከለኛ ኩባያ)
  • 80 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2 አነስተኛ ኩባያ)
  • 9 g የተከተፈ ቃሪያ (0.5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 4 ግራም ጨው (ለወጡ) (0.5 የሻይ ማንኪያ)
  • 70 ግራም ዘይት (2 አነስተኛ ኩባያ)
  • 950 ሚሊ ውሃ (ለወጡ) (0.95 ሊትር)
  • 350 ግራም ቆጮ (1.5 ትልቅ ኩባያ)
  • 50 ግራም ቂቤ (8 የሾርባ ማንኪያ)
  • 2 ግራም ጨው (ለቆጮው) (0.5 አነስተኛ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1ቦሎቄውን በ2 ሊትር ውሃ ውስጥ ለ100 ደቂቃ መቀቀል፤ ጎመኑን በ500 ሚሊ ውሃ ለ11 ደቂቃ ለብቻው ማፍላት።
  2. 2ሽንኩርት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ15 ደቂቃ ማቁላላት።
  3. 3የበሰለውን ቦሎቄ ጨምሮ ለ30 ደቂቃ ማብሰል፤ ጨው ጨምሮ ማውጣት።
  4. 4ለቆጮው፡ ቆጮውን በጋለ ምጣድ ላይ ያለ ቅባት ለ5 ደቂቃ ማብሰል፤ ጨውና የቀለጠ ቅቤ ጨምሮ እስኪፈረካከስ ለ5 ደቂቃ ማሸት።
  5. 5አቀራረብ፡ የበሰለውን ቆጮ መሃሉን በመብሳት የተሰራውን ወጥ መሃል ላይ ማፍሰስ፤ በቆጮው ሸፍኖ በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች