የድብልቅ ማሽላ ገንፎ በዘይት፦ ካሎሪ እና አሰራር
Ye'dibilik Mashila Genfo Be'zeit
የጾም ምግብኢትዮጵያዊቁርስ24 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 150 ግራም የተፈተገ የቀይ ማሽላ ዱቄት (2 መካከለኛ ኩባያ)
- 150 ግራም የተፈተገ የነጭ ማሽላ ዱቄት (2 መካከለኛ ኩባያ)
- 1200 ሚሊ ውሃ (1.2 ሊትር)
- 8 ግራም ጨው (1.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 60 ግራም ዘይት (10 የሾርባ ማንኪያ)
- 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1የቀይና የነጭ ማሽላ ዱቄቱን በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ መንፋት።
- 2ውሃውን ለ7 ደቂቃ ማፍላት።
- 3ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
- 5የተቀመጠውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እያከሉ ድስቱን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ16 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ሳህኑን በዘይት መቀባትና ገንፎውን ሳህን ላይ ማድረግ።
- 7ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን መብሳት።
- 8የሞቀውን ዘይት ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስና በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025