እንጀራ ድርቆሽ ፍርፍር፦ ካሎሪ እና አሰራር

Enjera Dirkosh Ferfer

የጾም ምግብኢትዮጵያዊቁርስመክሰስ20 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 215 ግራም የደረቀና የተፈጨ የነጭ ጤፍ ድርቆሽ (4 ትላልቅ ኩባያ)
  • 75 ግራም በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (ግማሽ ትልቅ ኩባያ)
  • 100 ግራም ያልተላጠ ቲማቲም (1 መካከለኛ ኩባያ)
  • 30 ግራም በርበሬ (3 የሾርባ ማንኪያ)
  • 10 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 60 ግራም ዘይት (10 የሾርባ ማንኪያ)
  • 700 ሚሊ ውሃ (0.7 ሊትር)

አሰራሩ

  1. 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን በዝቅተኛ እሳት ወርቃማ እስኪሆን ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2እንዳይዝ ትንሽ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማማሰል።
  3. 3ዘይት ጨምሮ አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ እስኪበስል ለ4 ደቂቃ ማማሰል።
  5. 5በርበሬ ጨምሮ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6የቀረውን ውሃ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  7. 7ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማፍላት።
  8. 8የተፈተፈተውን ድርቆሽ ወጡ ላይ ጨምሮ በሚገባ ማደባለቅ።
  9. 9አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ1 ደቂቃ አብስሎ ማውጣት።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች