የበሬ ስጋ ወጥ በአልጫ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Ye'bere Siga Wot, Alicha
ኢትዮጵያዊምሳእራት55 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 500 ግራም የተከተፈ የበሬ ስጋ (2.5 ትላልቅ ኩባያ)
- 135 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (0.75 ትልቅ ኩባያ)
- 130 ግራም ዘይት (1.5 መካከለኛ ኩባያ)
- 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 25 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (6 አነስተኛ ማንኪያ)
- 880 ሚሊ ውሃ (0.88 ሊትር)
- 3 ግራም እርድ (1 የሻይ ማንኪያ)
- 15 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (5 አነስተኛ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
- 2እርድ ጨምሮ እንዳይዝ ጥቂት ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ስጋውን ጨምሮ እሳቱን ቀንሶ ለ29 ደቂቃ ማንተክተክ።
- 5ውሃ ጨምሮ ለ10 ደቂቃ ማፍላት፤ (እንደ ምርጫ ቅቤ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል)።
- 6ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ቃሪያ ጨምሮ አዋህዶ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025