የበቆሎ እና የፉርኖ ዱቄት ገንፎ በቂቤ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Ye'bekolo ena Ye'furno Duket Genfo Be'kibe
ኢትዮጵያዊቁርስ29 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 250 ግራም የበቆሎ ዱቄት (9 አነስተኛ ኩባያ)
- 250 ግራም የፉርኖ ዱቄት (4 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
- 700 ሚሊ ውሃ (0.7 ሊትር)
- 68 ግራም ቂቤ (11.5 የሾርባ ማንኪያ)
- 20 ግራም በርበሬ (2 የሾርባ ማንኪያ)
- 240 ግራም እርጎ (12 የሾርባ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ የበቆሎ እና የፉርኖ ዱቄቱን መንፋት።
- 2በማብሰያ ድስት ውስጥ ውሃ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
- 3ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማፍላት።
- 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
- 5እንዳይጓጉል ያለማቋረጥ እያማሰሉ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
- 6የተቀመጠውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እየጨመሩ ድስቱን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ15 ደቂቃ ማብሰል።
- 7ሳህኑን በቅቤ መቀባትና ገንፎውን ሳህኑ ላይ ማድረግ።
- 8ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን በማንኪያ መብሳት።
- 9የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስ፤ በዙሪያው እርጎ አድርጎ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025