የአተር ሽሮ ተጋቢኖ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Ye'ater Shiro Tegabino
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት38 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 100 ግራም የአተር ሽሮ ዱቄት (3 አነስተኛ ኩባያ)
- 130 ግራም ዘይት (1.5 መካከለኛ ኩባያ)
- 100 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ኩባያ)
- 15 ግራም በርበሬ (1.5 የሻይ ማንኪያ)
- 145 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (5.25 የሻይ ማንኪያ)
- 10 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 7 ግራም ጨው (1 የሻይ ማንኪያ)
- 1000 ሚሊ ውሃ (1 ሊትር)
- 14 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (2 የሻይ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 2ዘይት ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ በርበሬ ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ቲማቲም ጨምሮ ለ5 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ውሃ ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማፍላት።
- 5የአተሩን ሽሮ እንዳይጓጉል እያማሰሉ ቀስ በቀስ በመነስነስ ለ14 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 7ቃሪያ ጣል አድርጎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025