የአተር፣ ሽምብራ እና የጓያ ተጋቢኖ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Ye'ater, Shimbra ena Guaya Shiro Tegabino
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት41 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 75 ግራም የአተር ሽሮ ዱቄት (5 የሾርባ ማንኪያ)
- 45 ግራም የሽምብራ ሽሮ ዱቄት (3 የሾርባ ማንኪያ)
- 30 ግራም የጓያ ሽሮ ዱቄት (2 የሾርባ ማንኪያ)
- 75 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (0.5 ትልቅ ኩባያ)
- 120 ግራም ዘይት (1.5 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 14 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 የሾርባ ማንኪያ)
- 3 ግራም የተፈጨ ዝንጅብል (0.5 የሻይ ማንኪያ)
- 1300 ሚሊ ውሃ (1.3 ሊትር)
- 8 ግራም ጨው (1.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)
- 150 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (1.5 መካከለኛ ኩባያ)
- 7 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (0.5 የሾርባ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
- 2ዘይት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ቲማቲም ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 3በርበሬ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ውሃ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
- 5የተደባለቀውን ሽሮ እንዳይጓጉል እያማሰሉ ቀስ በቀስ በመነስነስ ለ18 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ጨው ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 7ቃሪያ ጣል አድርጎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025