የአተር፣ የሽምብራ እና የባቄላ ሽሮ ወጥ በቀይ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'ater, Shimbra ena Bakela Shiro Wot, Keye

የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት34 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 40 ግራም የአተር ሽሮ ዱቄት (1.25 አነስተኛ ኩባያ)
  • 20 ግራም የሽምብራ ሽሮ ዱቄት (3.5 የሻይ ማንኪያ)
  • 40 ግራም የባቄላ ሽሮ ዱቄት (1.25 አነስተኛ ኩባያ)
  • 100 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 100 ግራም ዘይት (1.25 መካከለኛ የቡና ስኒ)
  • 12 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (3 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 5 ግራም የተፈጨ ዝንጅብል (1 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 800 ሚሊ ውሃ (0.8 ሊትር)
  • 15 ግራም ጨው (3 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2ዘይት ጨምሮ ለ5 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3በርበሬ ጨምሮ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4ውሃ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
  5. 5የተደባለቀውን ሽሮ እንዳይጓጉል እያማሰሉ ቀስ በቀስ በመነስነስ ለ15 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰልና በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች