የአተር፣ የሽምብራ እና የባቄላ ተጋቢኖ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'ater, Shimbra ena Bakela Shiro Tegabino

የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት34 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 40 ግራም የአተር ሽሮ ዱቄት (1.25 አነስተኛ ኩባያ)
  • 20 ግራም የሽምብራ ሽሮ ዱቄት (3.5 የሻይ ማንኪያ)
  • 40 ግራም የባቄላ ሽሮ ዱቄት (1.25 አነስተኛ ኩባያ)
  • 147 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1 ትልቅ ኩባያ)
  • 105 ግራም ዘይት (3 አነስተኛ ኩባያ)
  • 14 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 5 ግራም የተፈጨ ዝንጅብል (1 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 800 ሚሊ ውሃ (0.8 ሊትር)
  • 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 5 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (0.5 አነስተኛ ኩባያ)

አሰራሩ

  1. 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2ዘይት ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ በርበሬ ጨምሮ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4ውሃ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
  5. 5የተደባለቀውን ሽሮ እንዳይጓጉል ያለማቋረጥ እያማሰሉ ቀስ በቀስ በመነስነስ ለ16 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  7. 7ቃሪያ ጣል አድርጎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች