አንጮቴ ወጥ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'anchote Wot

የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት319 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 1006 ግራም ጥሬ አንጮቴ (7 ትላልቅ ኩባያ)
  • 8000 ሚሊ ውሃ (አንጮቴውን ለመቀቀል) (8 ሊትር)
  • 80 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ የቡና ስኒ)
  • 124 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2 መካከለኛ ኩባያ)
  • 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 1690 ሚሊ ውሃ (ለወጡ) (1.69 ሊትር)
  • 5 ግራም እርድ (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 15 ግራም የተፈጨ ዝንጅብል (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 15 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1አንጮቴውን በ8 ሊትር ውሃ ውስጥ ጥዶ ለ4 ሰዓት በከፍተኛ እሳት መቀቀል።
  2. 2የበሰለውን አንጮቴ ልጦ በደቃቁ ካሬ (ዳይስ) ቅርጽ መክተፍ።
  3. 3በሌላ ድስት ሽንኩርቱን ለ6 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4እርድ ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ እንዳይዝ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
  5. 5ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ጨምሮ ለ6 ደቂቃ ማብሰል፤ የተከተፈውን አንጮቴ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6የቀረውን ውሃ ጨምሮ ለ50 ደቂቃ ማብሰል።
  7. 7ጨው ጨምሮ ለ4 ደቂቃ አብስሎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች