የአጃ እና የገብስ ገንፎ በቂቤ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Ye'aja ena Ye'gebs Genfo Be'kibe

ኢትዮጵያዊቁርስ15 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 150 ግራም የሙሉ አጃ ዱቄት (2.25 መካከለኛ ኩባያ)
  • 150 ግራም የነጭ ገብስ ዱቄት (1.5 ትልቅ ኩባያ)
  • 800 ሚሊ ውሃ (0.8 ሊትር)
  • 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 60 ግራም ቂቤ (10 የሾርባ ማንኪያ)
  • 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ የአጃ እና የገብስ ዱቄቱን መንፋት።
  2. 2ውሃ በማብሰያ ውስጥ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
  3. 3ጨው ጨምሮ ለ1 ተጨማሪ ደቂቃ ማፍላት።
  4. 41 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይቋጥር ያለማቋረጥ ማማሰል።
  5. 5የተቀመጠውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እየጨመሩ ማብሰያውን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ12 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ሳህኑን በቅቤ/ዘይት ቀብቶ ገንፎውን ሳህን ላይ ማድረግ።
  7. 7ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና መሃሉን በማንኪያ መብሳት።
  8. 8የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስና በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች