ያልተፈተገ ነጭ በቆሎ ቂጣ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Yaltefetege Nech Bekolo Qita
የጾም ምግብኢትዮጵያዊቁርስመክሰስ10 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 300 ግራም የነጭ በቆሎ ዱቄት (5 መካከለኛ ኩባያ)
- 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 250 ሚሊ ውሃ (0.25 ሊትር)
አሰራሩ
- 1የበቆሎውን ዱቄት ወደ ሳህን ውስጥ መንፋት።
- 2ጨውና ውሃ ጨምሮ ሊጡ እስኪለሰልስ ለ5 ደቂቃ ያህል ማሸት።
- 3ምጣዱን ለ5 ደቂቃ ያህል ማሞቅ።
- 4ሊጡን አድቦ በጋለው ምጣድ ላይ በክብ ቅርጽ ማስተካከል።
- 5ክድኖ ወርቃማ እስኪሆን ለ5 ደቂቃ ያህል መጋገር።
- 6ቂጣውን ገልብጦ ለሌላ 5 ደቂቃ መጋገር።
- 7ከምጣዱ አውጥቶ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025