ቲማቲም ለብለብ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Timatim Lebeleb

የጾም ምግብኢትዮጵያዊቁርስመክሰስምሳ17 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 224 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (2.25 መካከለኛ ኩባያ)
  • 7 ግራም በርበሬ (3.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 10 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 50 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1.25 አነስተኛ ኩባያ)
  • 40 ግራም ዘይት (0.5 መካከለኛ የቡና ስኒ)
  • 3 ግራም ጨው (0.5 የሻይ ማንኪያ)
  • 17 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 100 ሚሊ ውሃ (0.1 ሊትር)

አሰራሩ

  1. 1ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2በርበሬ ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ እንዳያር ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማቁላላት።
  5. 5ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ፍሬው የወጣለት የተከተፈ ቃሪያ ጨምሮ አዋህዶ በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች