ጥህሎ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Tihillo

ኢትዮጵያዊምሳእራት40 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 150 ግራም የደረቀ የበሬ ስጋ (ቋንጣ) (1 ትልቅ ኩባያ)
  • 150 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (1.5 መካከለኛ ኩባያ)
  • 1 ግራም መከለሻ (ግማሽ አነስተኛ ማንኪያ)
  • 30 ግራም በርበሬ (3 የሾርባ ማንኪያ)
  • 7 ግራም ጨው (ለወጡ) (1 የሻይ ማንኪያ)
  • 80 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ የቡና ስኒ)
  • 24 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (6 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 30 ግራም ቅቤ (5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 500 ሚሊ ውሃ (ለወጡ) (0.5 ሊትር)
  • 200 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 303 ግራም የበሶ ዱቄት (3 ትላልቅ ኩባያ)
  • 430 ሚሊ ውሃ (ለሊጡ) (0.43 ሊትር)
  • 11 ግራም ጨው (ለሊጡ) (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 4 ግራም የኮረሪማ ዱቄት (2 አነስተኛ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1ሽንኩርቱን ለ6 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2በርበሬ ጨምሮ እንዳይዝ ጥቂት ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3ቲማቲም ጨምሮ ለ15 ደቂቃ ማብሰል፤ ቋንጣውን ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4መከለሻ፣ ጨው እና ቅቤ ጨምሮ ለ2 ደቂቃ አብስሎ ማውጣት።
  5. 5ለሊጡ፡ የበሶ ዱቄቱን ከውሃ ጋር ቀስ በቀስ እያዋሃዱ በሚገባ ማሸትና በደቃቁ ማድበልበል።
  6. 6ወጡን መሃል ላይ አድርጎ የተድበለበሉትን የበሶ ኳሶች በዙሪያው በመደርደር በስንጣር እየወጉ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች