ጥብስ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Tibs
ኢትዮጵያዊምሳእራት14 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 395 ግራም የተከተፈ የበሬ ስጋ (2 ትላልቅ ኩባያ)
- 118 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1 ትልቅ ኩባያ)
- 30 ግራም ዘይት (5 የሾርባ ማንኪያ)
- 22 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 አነስተኛ ኩባያ)
- 22 ግራም ቂቤ (3.5 የሾርባ ማንኪያ)
- 15 ግራም ሚጥሚጣ (1.5 የሾርባ ማንኪያ)
- 6 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 1 ግራም ኮረሪማ (0.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 88 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (1.25 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 4 ግራም ሮዝመሪ (የጥብስ ቅጠል) (1 የሾርባ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1የበሬውን ስጋ በደቃቁ መክተፍ።
- 2መጥበሻ ላይ ዘይት አሙቆ ስጋውን ጨምሮ ያለማቋረጥ እያማሰሉ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ሽንኩርቱን ጨምሮ ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ቲማቲም ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ቃሪያ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 5ኮረሪማ፣ ቅቤ እና ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 6የጥብስ ቅጠል (ሮዝመሪ) ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ ከእሳት ማውጣት።
- 7በሙቀቱ ከእንጀራ እና ከሚጥሚጣ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025