ስንግ ቃሪያ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Sineg Qarya
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት5 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 201 ግራም ቃሪያ (6 ትላልቅ ቃሪያዎች)
- 65 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1 መካከለኛ ኩባያ)
- 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 108 ግራም ፍሬው የወጣለት የተከተፈ ቲማቲም (1 መካከለኛ ቲማቲም)
- 40 ግራም ዘይት (0.5 መካከለኛ የቡና ስኒ)
አሰራሩ
- 1ሽንኩርት፣ ቲማቲም እና ጨው በሳህን ውስጥ ማደባለቅ።
- 2መጥበሻ ላይ ዘይት አሙቆ ድብልቁን በዝቅተኛ እሳት ለ1 ደቂቃ ማቁላላት።
- 3ቃሪያውን በመሃል ሰንጥቆ ፍሬውን ማውጣት።
- 4የተዘጋጀውን የቲማቲምና ሽንኩርት ድብልቅ በቃሪያው ውስጥ መሙላትና ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025