ሽሮ ወጥ በእንቁላል፦ ካሎሪ እና አሰራር
Shiro Wot Be'enqulale
ኢትዮጵያዊምሳእራት26 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 80 ግራም የአተር ሽሮ ዱቄት (1.5 አነስተኛ ኩባያ)
- 75 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 15 ግራም በርበሬ (1.5 የሾርባ ማንኪያ)
- 67 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (3 የሾርባ ማንኪያ)
- 71 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (1 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 1000 ሚሊ ውሃ (1 ሊትር)
- 60 ግራም የዶሮ እንቁላል (1 ትልቅ እንቁላል)
- 5 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 አነስተኛ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 2ዘይት ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ቲማቲም ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 3በርበሬ ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ውሃ ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማፍላት።
- 5የአተሩን ሽሮ እንዳይጓጉል እያማሰሉ ቀስ በቀስ በመነስነስ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
- 6የተመታውን እንቁላል ጨምሮ እንቁላሉ እንዳይፈረካከስ ቀስ እያሉ በማማሰል ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 7ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ አብስሎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025