ፓስታ በቲማቲም ስጎ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Pasta Be'timatim Sego
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት54 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 350 ግራም ፓስታ
- 1500 ሚሊ ውሃ (ፓስታውን ለመቀቀል) (1.5 ሊትር)
- 182 ግራም ዘይት (1 ትልቅ ኩባያ)
- 147 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1 ትልቅ ኩባያ)
- 20 ግራም በርበሬ (2 የሾርባ ማንኪያ)
- 204 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (2 መካከለኛ ኩባያ)
- 14 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 የሾርባ ማንኪያ)
- 8 ግራም ጨው (1.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 19 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 አነስተኛ ኩባያ)
- 600 ሚሊ ውሃ (ለሶሱ ማዘጋጃ) (0.6 ሊትር)
- 35 ግራም የታሸገ ቲማቲም ድልህ (1 የሾርባ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1በድስት ውስጥ 1500 ሚሊ ውሃ አፍልቶ ፓስታውን ለ10 ደቂቃ መቀቀል፤ አውጥቶ አጥልሎ ማስቀመጥ።
- 2ሽንኩርቱን ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 3በርበሬ ጨምሮ ጥቂት ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 4የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
- 5የታሸገ ቲማቲም ድልህ ጨምሮ እንዳይዝ ውሃ ጠብ እያደረጉ ያለማቋረጥ እያማሰሉ ለ23 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
- 7ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 8የበሰለውን ስጎ በፓስታው ላይ ጨምሮ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025