ምስር ወጥ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Misir Wat
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት48 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 250 ግራም የክክ ምስር (2.5 መካከለኛ ኩባያ)
- 90 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ኩባያ)
- 95 ግራም ዘይት (0.5 ትልቅ ኩባያ)
- 34 ግራም በርበሬ (1 አነስተኛ ኩባያ)
- 80 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (1.5 አነስተኛ ኩባያ)
- 10 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 የሻይ ማንኪያ)
- 13 ግራም ጨው (2 የሻይ ማንኪያ)
- 1700 ሚሊ ውሃ (1.7 ሊትር)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
- 2ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል፤ በርበሬ ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ እንዳያር ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ቲማቲም ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 4የምስሩን ክክ ጨምሮ ውሃ እያከሉ እንዳይዝ ለ27 ደቂቃ ማብሰል።
- 5የቀረውን ውሃ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማፍላት።
- 6ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ አብስሎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025