ምስር ክክ ወጥ በአልጫ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Misir Kik Wot, Alicha
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት44 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 250 ግራም የክክ ምስር (2.5 መካከለኛ ኩባያ)
- 80 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2 አነስተኛ ኩባያ)
- 100 ግራም ዘይት (1.25 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 5 ግራም እርድ (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 10 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 15 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 ትልቅ ማንኪያ)
- 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
- 1750 ሚሊ ውሃ (1.75 ሊትር)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 2እርድ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
- 3የምስሩን ክክ ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ እንዳይዝ ለ20 ደቂቃ ማብሰል።
- 4የቀረውን ውሃ ጨምሮ ምስሩ በሚገባ እስኪዋሃድ ለ10 ደቂቃ ማፍላት።
- 5ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ቃሪያ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025