ምንቸት ወጥ በቀይ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Minchet Wot, Keye
ኢትዮጵያዊምሳእራት43 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 400 ግራም የተፈጨ የበሬ ስጋ (2 ትላልቅ ኩባያ)
- 140 ግራም ዘይት (4 አነስተኛ ኩባያ)
- 240 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (6 አነስተኛ ኩባያ)
- 50 ግራም በርበሬ (5 የሾርባ ማንኪያ)
- 273 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (4 መካከለኛ የቡና ስኒ)
- 20 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
- 30 ግራም ቂቤ (5 የሾርባ ማንኪያ)
- 1200 ሚሊ ውሃ (1.2 ሊትር)
- 3 ግራም መከለሻ (1.5 አነስተኛ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ6 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 2በርበሬ ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ7 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ቲማቲም ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
- 4የተፈጨውን ስጋ ጨምሮ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
- 5የቀረውን ውሃ ጨምሮ ለ7 ደቂቃ ማፍላት።
- 6መከለሻ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ጨው ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 7ቅቤ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025