ምላስ ሰምበር፦ ካሎሪ እና አሰራር

Milas Sember

ኢትዮጵያዊቁርስምሳ38 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 377 ግራም የተከተፈ ሰንበር (2 ትላልቅ ኩባያ)
  • 100 ግራም የተከተፈ የበሬ ምላስ (0.5 ኩባያ)
  • 220 ግራም የተከተፈ የበሬ ስጋ (4.5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 223 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1.5 ትልቅ ኩባያ)
  • 32 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (2.5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 26 ግራም የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት (2 የሾርባ ማንኪያ)
  • 6 ግራም ጨው (1 የሻይ ማንኪያ)
  • 18 ግራም ሚጥሚጣ (0.5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 75 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ የቡና ስኒ)
  • 9 ግራም ሰናፍጭ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 15 ግራም አዋዜ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 15 ግራም ቂቤ (4 የሻይ ማንኪያ)
  • 220 ሚሊ ውሃ

አሰራሩ

  1. 1ሰንበሩን፣ ምላሱን እና የበሬ ስጋውን በስሱ መክተፍ።
  2. 2ሰንበሩን ድስት ውስጥ ጨምሮ ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3ምላሱን ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ18 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4የበሬ ስጋውን ጨምሮ ለ6 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
  5. 5ሽንኩርትና ቃሪያ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ጨው እና ቅቤ ጨምሮ ለ2 ደቂቃ አብስሎ ከእሳት ማውጣት።
  7. 7በሙቀቱ ከእንጀራ እና ከአዋዜ፣ ሰናፍጭና ሚጥሚጣ ማባያ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች