ቀይ አይብ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Keye Ayib
ኢትዮጵያዊምሳእራትመክሰስ20 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 680 ግራም አይብ (5 ትላልቅ ኩባያ)
- 0.5 ግራም የአብሽ ዱቄት (0.25 አነስተኛ ማንኪያ)
- 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 10 ግራም ሚጥሚጣ (1 የሾርባ ማንኪያ)
- 50 ግራም ቂቤ (8 የሾርባ ማንኪያ)
- 2 ግራም ኮረሪማ (1 አነስተኛ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1አይቡን በወንፊት ላይ አድርጎ ውሃውን ለጥቂት ደቂቃዎች ማጠንፈፍ።
- 2አይቡን በማንኪያ በሚገባ ማሸት/ማለስለስ።
- 3አብሽ፣ ጨው፣ ሚጥሚጣ እና ኮረሪማ ጨምሮ በእጅ ወይም በትልቅ ማንኪያ በሚገባ ማዋሃድ።
- 4የቀለጠውን ቅቤ በላዩ ላይ አፍሶ በሚገባ ማደባለቅ።
- 5ጣባ ላይ አውጥቶ የቀረውን ቅቤ ከላይ በማፍሰስ ከቆጮ ቂጣ ወይም ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025