እንቁላል ፍርፍር፦ ካሎሪ እና አሰራር

Inkulal Firfir

ኢትዮጵያዊቁርስ7 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 210 ግራም የዶሮ እንቁላል (4 ትላልቅ እንቁላሎች)
  • 3 ግራም ጨው (0.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 30 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1.5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 10 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 21 ግራም ዘይት (3 የሾርባ ማንኪያ)
  • 38 ግራም ፍሬው የወጣለት የተከተፈ ቲማቲም (1.25 የሾርባ ማንኪያ)
  • 6 ግራም ቂቤ (1 የሾርባ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1መጥበሻ ላይ ዘይት አድርጎ ለ1 ደቂቃ ማሞቅ።
  2. 2የተከተፈ ሽንኩርት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማቁላላት።
  3. 3የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4እንቁላል እና ጨው በሳህን ውስጥ መምታት።
  5. 5የተመታውን እንቁላል መጥበሻ ላይ ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6የተከተፈ ቃሪያ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  7. 7ከእሳት አውርዶ ቅቤ ጨምሮ በሙቀቱ ከዳቦ ወይም ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች