ጎመን በስጋ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Gomen Besiga
ኢትዮጵያዊምሳእራት52 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 127 ግራም የተከተፈ የበሬ ስጋ (1.25 መካከለኛ ኩባያ)
- 250 ግራም የተከተፈ የጎመን ቅጠል (3 ትላልቅ ኩባያ)
- 100 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2.5 መካከለኛ ኩባያ)
- 10 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 25 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (2 የሾርባ ማንኪያ)
- 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
- 30 ግራም ቂቤ (5 የሾርባ ማንኪያ)
- 1000 ሚሊ ውሃ (1 ሊትር)
- 82 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ ኩባያ)
- 3 ግራም ኮረሪማ (0.5 የሻይ ማንኪያ)
አሰራሩ
- 1ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ3 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 2የበሬ ስጋውን ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ጎመኑን ጨምሮ ለ20 ደቂቃ ማብሰል።
- 5ኮረሪማ ጨምሮ ለ18 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ጨው እና ቅቤ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ቃሪያ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ ከእሳት ማውጣትና በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025