ገንፎ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Genfo

ኢትዮጵያዊቁርስ17 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 300 ግራም የነጭ ገብስ ዱቄት (3 ትላልቅ ኩባያ)
  • 10 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 1150 ሚሊ ውሃ (1.15 ሊትር)
  • 70 ግራም ቂቤ (2 አነስተኛ ኩባያ)
  • 10 ግራም በርበሬ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 90 ግራም የአረንጓዴ ቃሪያ ዳጣ/ቆጭቆጫ (1.5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 150 ግራም እርጎ (0.75 ትልቅ ኩባያ)

አሰራሩ

  1. 1የገብሱን ዱቄት በሰፌድ ወይም በትሪ ላይ መንፋት።
  2. 2ውሃውን በማብሰያ ውስጥ ለ5 ደቂቃ ማፍላትና ጨው መጨመር።
  3. 31 ኩባያ የፈላ ውሃ ቀንሶ ማስቀመጥ፤ ከዚያም ዱቄቱን የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ እንዳይጓጉል ያለማቋረጥ ማማሰል።
  4. 4የተቀመጠውን የፈላ ውሃ ቀስ በቀስ እየጨመሩ ማብሰያውን መክደንና አልፎ አልፎ እያማሰሉ ለ12 ደቂቃ ማብሰል።
  5. 5የቀረበበትን ሳህን በቅቤ መቀባትና ገንፎውን ሳህኑ ላይ ማድረግ።
  6. 6ገንፎውን ክብ ቅርጽ ማሲያዝ እና በማንኪያ መሃሉን መብሳት (ጉድጓድ ማውጣት)።
  7. 7የቀለጠውን ቅቤ ከበርበሬ ጋር አዋህዶ መሃሉ ላይ ማፍሰስ።
  8. 8በዙሪያው እርጎ እና ቆጭቆጫ አድርጎ በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች