እንቁላል በስጋ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Enqulal Be' Siga

ኢትዮጵያዊቁርስ14 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 311 ግራም የዶሮ እንቁላል (6 ትላልቅ እንቁላሎች)
  • 184 ግራም በስሱ የተከተፈ የበሬ ስጋ (3.5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 70 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (0.5 ትልቅ ኩባያ)
  • 13 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 የሾርባ ማንኪያ)
  • 125 ግራም ፍሬው የወጣለት የተከተፈ ቲማቲም (1.25 መካከለኛ ኩባያ)
  • 30 ግራም ዘይት (5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 30 ግራም ቂቤ (5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 40 ሚሊ ውሃ
  • 5 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1ማብሰያ ድስቱን አሙቆ ሽንኩርቱን በመካከለኛ እሳት ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
  2. 2ዘይት ጨምሮ እስኪለሰልስ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3የበሬ ስጋውን ጨምሮ ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማቁላላት።
  5. 5በሳህን ውስጥ እንቁላልና ጨው አንድ ላይ መምታት።
  6. 6የተመታውን እንቁላል ድስቱ ውስጥ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  7. 7የተከተፈ ቃሪያ እና ቅቤ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አዋህዶ ከእሳት ማውጣት።
  8. 8በሙቀቱ ከዳቦ ወይም ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች