እንጀራ ፍርፍር በስጋ ቀይ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Enjera Ferfer Be'siga, Keye
ኢትዮጵያዊቁርስምሳእራት44 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 349 ግራም የነጭ ጤፍ እንጀራ (1 መካከለኛ)
- 136 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (3.33 አነስተኛ ኩባያ)
- 61 ግራም ዘይት (10 የሾርባ ማንኪያ)
- 31 ግራም በርበሬ (3 የሾርባ ማንኪያ)
- 168 ግራም የተከካ የበሬ ስጋ (3.33 አነስተኛ ኩባያ)
- 14 ግራም ቅቤ (2.5 የሾርባ ማንኪያ)
- 2 ግራም ኮረሪማ (ግማሽ አነስተኛ ማንኪያ)
- 20 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (5 አነስተኛ ማንኪያ)
- 11 ግራም ጨው (2 አነስተኛ ማንኪያ)
- 500 ሚሊ ውሃ (0.5 ሊትር)
- 126 ግራም የተከተፈ ቲማቲም (0.25 መካከለኛ ኩባያ)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን በዝቅተኛ እሳት ወርቃማ እስኪሆን ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 2እንዳይዝ ጥቂት ውሃ እየጨመሩ ማማሰል።
- 3ዘይት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 4የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ ለ8 ደቂቃ አልፎ አልፎ እያማሰሉ ማብሰል።
- 5በርበሬ ጨምሮ እንዳያር ትንሽ ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ10 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 7የበሬ ስጋውን ጨምሮ በሚገባ በማዋሃድ ለ17 ደቂቃ ማብሰል።
- 8ኮረሪማ ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 9ውሃ ጨምሮ ለ3 ደቂቃ እንዲፈላ ማድረግ።
- 10ጨው እና ቅቤ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማፍላት።
- 11የተቆራረሰ እንጀራ ወጡ ላይ ጨምሮ በሚገባ ማደባለቅ።
- 12ለ1 ደቂቃ አልፎ አልፎ እያማሰሉ አብስሎ ማውጣትና በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025