ዶሮ አሩስቶ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Doro Arusto

ኢትዮጵያዊምሳእራት67 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 2896 ግራም ሙሉ የዶሮ ስጋ ከነቆዳውና አጥንቱ
  • 115 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (3 አነስተኛ ኩባያ)
  • 30 ግራም በርበሬ (3 የሾርባ ማንኪያ)
  • 65 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (4.5 የሾርባ ማንኪያ)
  • 16 ግራም የተከተፈ የጥብስ ቅጠል/ሮዝመሪ (1 መካከለኛ ኩባያ)
  • 80 ግራም የፉርኖ ዱቄት (6 የሾርባ ማንኪያ)
  • 5 ግራም ቁንዶ በርበሬ (2.5 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 220 ግራም ዘይት (2.5 መካከለኛ ኩባያ)
  • 25 ግራም ጨው (5 አነስተኛ ማንኪያ)

አሰራሩ

  1. 1ዶሮውን በሚገባ አጥቦ ማጽዳት።
  2. 2በትልቅ ሳህን ውስጥ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ የጥብስ ቅጠል፣ በርበሬ፣ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ እና ዘይት አንድ ላይ ማደባለቅ።
  3. 3ዶሮውን በፉርኖ ዱቄት በሚገባ ማዳረስ።
  4. 4ዶሮውን በተዘጋጀው ማጣፈጫ ቅመም ውስጥ ነክሮ በደንብ ማሸት።
  5. 5የብረት መጋገሪያ ላይ አድርጎ ኦቨን ውስጥ ለ67 ደቂቃ ወርቃማ እስኪሆን መጥበስ።
  6. 6ከኦቨን አውጥቶ በሙቀቱ ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች