ድንች በጥቅል ጐመን፦ ካሎሪ እና አሰራር
Dinch Be'tikil Gomen
የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት50 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 390 ግራም የተላጠ የተከተፈ ድንች (2 ትላልቅ ኩባያ)
- 543 ግራም የተከተፈ ጥቅል ጎመን (12 መካከለኛ ኩባያ)
- 100 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (2.5 አነስተኛ ኩባያ)
- 60 ግራም ዘይት (10 የሾርባ ማንኪያ)
- 15 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (4 አነስተኛ ማንኪያ)
- 6 ግራም ጨው (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 21 ግራም የተከተፈ ቃሪያ (1 አነስተኛ ኩባያ)
- 700 ሚሊ ውሃ (0.7 ሊትር)
አሰራሩ
- 1ጥቅል ጎመኑን መክተፍ፣ ለብ ባለ የጨው ውሃ አጥቦ ማጠንፈፍ።
- 2ሽንኩርቱን በመካከለኛ እሳት ለ4 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 3ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 4ጥቅል ጎመኑን ጨምሮ ከስር ወደ ላይ እያገላበጡ ለ15 ደቂቃ ማብሰል።
- 5የተከተፈ ድንች ጨምሮ ቀስ እያሉ ማማሰል።
- 6200 ሚሊ ውሃ ጨምሮ ክድኖ ድንቹ እስኪበስል ለ27 ደቂቃ ማብሰል።
- 7ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል፤ ቃሪያ ጣል አድርጎ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025