ድንች በድፍን ምስር ወጥ፦ ካሎሪ እና አሰራር

Dinch Be'difin Misir Wot

የጾም ምግብኢትዮጵያዊምሳእራት100 ደቂቃ

ግብዓቶች

  • 324 ግራም ድፍን ምስር (3.25 መካከለኛ ኩባያ)
  • 134 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (3.5 አነስተኛ ኩባያ)
  • 90 ግራም ዘይት (0.5 ትልቅ ኩባያ)
  • 16 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (4 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 290 ግራም የተላጠ ድንች (2 ትላልቅ ኩባያ)
  • 16 ግራም ጨው (3 አነስተኛ ማንኪያ)
  • 21 ግራም በርበሬ (2 የሾርባ ማንኪያ)
  • 2500 ሚሊ ውሃ (2.5 ሊትር)

አሰራሩ

  1. 1በትልቅ ድስት ውስጥ 1.5 ሊትር ውሃና የተለቀመውን ድፍን ምስር ጨምሮ ለ60 ደቂቃ መቀቀል።
  2. 2በሌላ ድስት ሽንኩርቱን ወርቃማ እስኪሆን ለ2 ደቂቃ ማብሰል፤ ዘይት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
  3. 3ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ3 ደቂቃ ማብሰል፤ በርበሬ ጨምሮ ለ5 ደቂቃ ማብሰል።
  4. 4የተቀቀለውን ድፍን ምስር ከመረቁ ጋር አብሮ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማፍላት።
  5. 5የተከተፈውን ድንች ጨምሮ እስኪለሰልስ ለ26 ደቂቃ ማብሰል።
  6. 6ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ በሙቀቱ ከእንጀራ ጋር ማቅረብ።

የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025

ተመሳሳይ ምግቦች