ፓስታ በስጋ፦ ካሎሪ እና አሰራር
Spaghetti Bolognese
ምሳእራት49 ደቂቃ
ግብዓቶች
- 350 ግራም ፓስታ
- 1500 ሚሊ ውሃ (ፓስታውን ለመቀቀል) (1.5 ሊትር)
- 85 ግራም ዘይት (1 መካከለኛ ኩባያ)
- 147 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት (1 ትልቅ ኩባያ)
- 20 ግራም በርበሬ (2 የሾርባ ማንኪያ)
- 204 ግራም በደቃቁ የተከተፈ ቲማቲም (2 መካከለኛ ኩባያ)
- 14 ግራም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት (1 የሾርባ ማንኪያ)
- 10 ግራም ጨው (2 የሻይ ማንኪያ)
- 2 ግራም ቁንዶ በርበሬ (1 አነስተኛ ማንኪያ)
- 500 ሚሊ ውሃ (ለወጡ) (0.5 ሊትር)
- 35 ግራም የታሸገ የቲማቲም ድልህ (1 የሾርባ ማንኪያ)
- 200 ግራም የተፈጨ የበሬ ስጋ (1 ትልቅ ኩባያ)
አሰራሩ
- 1ማብሰያውን አሙቆ ሽንኩርቱን እስኪለሰልስና ቡናማ እስኪሆን ለ3 ደቂቃ ማብሰል።
- 2ዘይት ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 3የታሸገ ቲማቲም ድልህ ጨምሮ ለ1 ደቂቃ ማብሰል።
- 4በርበሬ ጨምሮ እንዳይዝ ጥቂት ውሃ ጠብ እያደረጉ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
- 5የተከተፈ ቲማቲም ጨምሮ እያማሰሉ ለ2 ደቂቃ ማብሰል።
- 6ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ለ6 ደቂቃ ማብሰል።
- 7የተፈጨውን የበሬ ስጋ ጨምሮ ለ15 ደቂቃ ማብሰል።
- 8ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ለ4 ደቂቃ ማብሰል።
- 9ጨው ጨምሮ ለ1 ደቂቃ አብስሎ ከእሳት ማውጣት።
- 10በሌላ ድስት ውስጥ 1500 ሚሊ ውሃ አፍልቶ ፓስታውን ጨምሮ ለ10 ደቂቃ መቀቀል።
- 11ፓስታውን አውጥቶ ውሃውን ማጥለልና በቀዝቃዛ ውሃ ማጠብ።
- 12የተሰራውን የስጋ ወጥ በፓስታው ላይ ጨምሮ በሚገባ በማዋሃድ በሙቀቱ ማቅረብ።
የአሰራር መመሪያ እና የንጥረ ነገር መረጃ፦ EPHI & FAO, Ethiopian Food Recipes 2025